ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 30:3-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ምርኮህን ይመልስልሃል፤ ይራራልሃልም፤ አንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስብሃል።

4. ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዝ እንኳ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከዚያ ይሰበስብሃል፤ መልሶም ያመጣሃል።

5. የአባቶችህ ወደሆነችው ምድር ያመጣሃል፤ አንተም ትወር ሳታለህ። ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ ያበዛሃልም።

6. አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ እንድትወደው፣ በሕይወትም እንድትኖር፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የአንተንና የዘርህን ልብ ይገርዛል።

7. አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያደርገዋል።

8. አንተም ተመልሰህ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቃለህ።

9. ከዚያም አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእጅህ ሥራ ሁሉና በወገብህ ፍሬ፣ በእንስሳትህ ግልገሎችና በምድርህ ሰብል እጅግ ያበለጽግሃል። በአባቶችህ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና።

10. ይህም የሚሆነው፣ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስትመለስ ነው።

11. በዛሬው ዕለት የምሰጥህ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከአንተ የራቀች አይደለችም።

12. “እንድንፈጽማት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ፣ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?” እንዳትል፣ በላይ በሰማይ አይደለችም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 30