ዳግመኛ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር (ያህዌ) በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።