ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 26:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በመሓላ ቃል በገባኸው መሠረት፣ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ባርክ።”

16. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይህን ሥርዐትና ሕግ ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ ያዝሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ ትፈጽመው ዘንድ ተጠንቀቅ።

17. እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ ኤሎሂም) እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፣ ሥርዐቱን፣ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት በዛሬዪቱ ዕለት ተናግረሃል።

18. እግዚአብሔር (ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ፣ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፣ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት ተናግሮአል፤

19. ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፣ በስም፣ በክብርም ከፍ እንደሚያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆን ተናግሮአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 26