ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 25:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩህ።

15. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፣ ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ።

16. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።

17. ከግብፅ በወጣህ ጊዜ፣ አማሌቅ በመንገድ በአንተ ላይ ያደረገብህን አስታውስ፤

18. ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፣ በጒዞ ላይ አግኝተውህ፣ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም (ኤሎሂም) አልፈሩም።

19. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ!

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 25