ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 21:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደሆነ ባይታወቅ፣

2. ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ ወጥተው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ።

3. ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፣

4. ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን ዐንገት ይስበሩ፤

5. እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጒዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 21