ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 19:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ተንኰለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ቢከስ፣

17. ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት፣ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ።

18. ፈራጆችም ጒዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ፣

19. በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

20. የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም።

21. ርኅራኄ አታድርግ፤ ሕይወት በሕይወት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር ይመለስ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 19