ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 18:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፣ “እንዳልሞት የአምላክህ የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ” ብለህ አምላክህን እግዚአብሔርን (ያህዌ ኤሎሂም) የጠየቅኸው ይህን ነውና።

17. እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለኝ፤ “የተናገሩት መልካም ነው፤

18. ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል።

19. ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፣ እኔ ራሴ በተጠያቂነት እይዘዋለሁ።

20. ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜ የሚናገርም ሆነ በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።”

21. አንተም በልብህ፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያልተናገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን?” ብትል፣

22. ነቢዩ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 18