ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 13:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት፣) ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣

7. በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላው ድረስ በዙሪያህ ያሉትን የአሕዛብ አማልክት እናምልክ ቢልህ፣

8. እሺ አትበለው፤ ወይም አታዳምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው።

9. ያለማመንታት ግደለው፤ እርሱንም ለመግደል በመጀመሪያ የአንተ እጅ፣ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይነሣ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 13