ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 13:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነቢይ ወይም ሕልም ዐላሚ ከመካከልህ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፣

2. የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፣ “አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው” ቢልህ፣

3. አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁ ነውና፣ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም ዐላሚውን አትስማ።

4. አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ተከተሉት፤ ፍሩት፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ታዘዙት፤ አገልግሉት፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።

5. ከግብፅ ባወጣችሁና ከባርነት ምድር በዋጃችሁ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ላይ እንድታምፁ ተናግሮአልና፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ እንድትመለሱ አድርጎአልና፣ ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ ስለዚህ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ።

6. የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት፣) ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣

7. በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላው ድረስ በዙሪያህ ያሉትን የአሕዛብ አማልክት እናምልክ ቢልህ፣

8. እሺ አትበለው፤ ወይም አታዳምጠው፤ አትራራለት፤ አትማረው፤ ወይም አትሸሽገው።

9. ያለማመንታት ግደለው፤ እርሱንም ለመግደል በመጀመሪያ የአንተ እጅ፣ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይነሣ።

10. የባርነት ምድር ከሆነው ከግብፅ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሊያርቅህ ፈልጎአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።

11. ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም ማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አያደርግም።

12. አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድ ትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች ባንዲቱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ብትሰማ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 13