ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 11:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ከዚያም የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቊጣ በላያችሁ ይነዳል፤ እርሱም ዝናብ እንዳይዘንብ፣ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።

18. እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ።

19. ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፣ መንገድ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣ ስለ እነዚሁ አጫውታቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 11