ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘዳግም 1:43-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላዳመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፤ በትዕቢታችሁ ወደ ኰረብታማዪቱ አገር ዘመታችሁ።

44. በነዚያ ኰረብቶች ላይ የሚኖሩት አሞራውያን ሊወጓችሁ ወጡ፤ እንደ ንብ ሰራዊትም ሆነው አባረሯችሁ፤ ከሴይር አንሥቶ እስከ ሔርማ ድረስ አሳደው መቷችሁ።

45. እናንተም ተመልሳችሁ መጥታችሁ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት አለቀሳችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ልቅሶአችሁን አልሰማም፤ አላዳመጣችሁምም።

46. ስለዚህ ያን ያህል ጊዜ በማጥፋት በቃዴስ ብዙ ቀን ቈያችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘዳግም 1