ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 4:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።

12. እንደ ገናም፣ “በሁለቱ የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅርንጫፎች ምንድን ናቸው?” አልሁት።

13. እርሱም፣ “ምን እንደሆኑ አታውቅምን?” አለኝ።እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።

14. እርሱም፣ “እነዚህ ሁለቱ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገልገል የተቀቡ ናቸው” አለኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 4