ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 2:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤

4. እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤

5. እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’

6. “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

7. “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 2