ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 2:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤

2. እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት።እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋትምን ያህል እንደሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።

3. ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤

4. እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤

5. እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’

6. “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

7. “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”

8. እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላልና፤ “ካከበረኝና በዘረፉአችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፣ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፤

9. እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

10. “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ ደስም ይበልሽ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

11. “በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 2