ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 11:8-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ።በጎቹ ጠሉኝ፤ እኔም፣ ሰለቸኋቸው፤

9. “እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉት ይጥፉ፤ የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።

10. ከዚያም ከአሕዛብ ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን ለማፍረስ፣ “ሞገስ” ብዬ የጠራሁትን በትሬን ወስጄ ሰበርሁት።

11. በዚያም ቀን ኪዳኑ ፈረሰ፤ ሲመለከቱኝ የነበሩትና የተጨነቁት በጎችም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ዐወቁ።

12. እኔም፣ “የሚበጅ መስሎ ከታያችሁ ዋጋ ዬን ክፈሉኝ፤ አይሆንም ካላችሁም ተውት” አልኋቸው፤ ስለዚህ ሠላሳ ብር ከፈሉኝ።

13. እግዚአብሔርም ሊከፍሉኝ የተስማሙበትን ጥሩ ዋጋ “በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው” አለኝ፤ እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው ግምጃ ቤት አስቀመጥሁት።

14. ከዚያም የእስራኤልንና የይሁዳን ወንድማማችነት በማፍረስ፣ “አንድነት” ብዬ የጠራሁትን ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።

15. እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “እንደ ገና የሰነፍ እረኛ ዕቃ ውሰድ፤

16. እነሆ፤ በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፤ የባዘነውን አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፤ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኰናውንም ሳይቀር ይቀለጣጥማል።

17. “መንጋውን ለሚተው፣ለማይረባ እረኛ ወዮለት!ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ትውጋው፤ክንዱ ፈጽማ ትስለል፤ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 11