ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 11:14-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ከዚያም የእስራኤልንና የይሁዳን ወንድማማችነት በማፍረስ፣ “አንድነት” ብዬ የጠራሁትን ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።

15. እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “እንደ ገና የሰነፍ እረኛ ዕቃ ውሰድ፤

16. እነሆ፤ በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሣለሁ፤ እርሱም የጠፋውን አያስብም፤ የባዘነውን አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ የዳነውንም አይቀልብም፤ ነገር ግን የሰባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኰናውንም ሳይቀር ይቀለጣጥማል።

17. “መንጋውን ለሚተው፣ለማይረባ እረኛ ወዮለት!ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ትውጋው፤ክንዱ ፈጽማ ትስለል፤ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 11