ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 11:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከዚያም ከአሕዛብ ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን ለማፍረስ፣ “ሞገስ” ብዬ የጠራሁትን በትሬን ወስጄ ሰበርሁት።

11. በዚያም ቀን ኪዳኑ ፈረሰ፤ ሲመለከቱኝ የነበሩትና የተጨነቁት በጎችም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ዐወቁ።

12. እኔም፣ “የሚበጅ መስሎ ከታያችሁ ዋጋ ዬን ክፈሉኝ፤ አይሆንም ካላችሁም ተውት” አልኋቸው፤ ስለዚህ ሠላሳ ብር ከፈሉኝ።

13. እግዚአብሔርም ሊከፍሉኝ የተስማሙበትን ጥሩ ዋጋ “በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው” አለኝ፤ እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው ግምጃ ቤት አስቀመጥሁት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 11