ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 10:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።

2. ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።

3. “ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት፣ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃልና፤በጦርነትም ጊዜ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 10