ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 7:55-71 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

55. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

56. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

57. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

58. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

59. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የፍደሱር ልጅ ገማልኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

60. በዘጠነኛው ቀን የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ስጦታውን አመጣ፤

61. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

62. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

63. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

64. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

65. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

66. በአሥረኛው ቀን የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ስጦታውን አመጣ፤

67. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

68. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

69. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

70. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

71. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 7