ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 7:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

15. ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

16. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

17. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

18. በሁለተኛው ቀን የይሳኮር አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ስጦታውን አመጣ፤

19. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

20. ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

21. ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣

22. ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣

23. እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ አምስት አውራ በግ፣ አምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው አምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሶገር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።

24. በሦስተኛው ቀን የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ስጦታውን አመጣ፤

25. ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቊርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 7