ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 6:20-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ከዚያም ካህኑ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ እነዚህም የተቀደሱ ናቸው። ከተወዘወዘው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር የተቀደሱ የካህኑ ድርሻ ይሆናሉ። ከዚህ በኋላ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት ይችላል።

21. “ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለሚሳል ናዝራዊ ሕጉ ይኸው ነው፤ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለመስጠት ቃል ለሚገባው ነገር እንደ ናዝራዊነቱ በተሳለው መሠረት መሆን አለበት። በናዝራዊነት ሕግ መሠረት የተሳለውን ስእለት መፈጸም ይገባዋል።’ ”

22. እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን አለው፤

23. “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሉአቸው፤

24. “ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ይጠብቅህም፤

25. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊቱን ያብራልህ፤ይራራልህም፤

26. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊቱን ይመልስልህ፤ሰላሙንም ይስጥህ።’ ”

27. “በዚህ ሁኔታ ስሜን በእስራኤላውያን ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 6