ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 34:14-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የሮቤል ነገድ ቤተ ሰቦች፣ የጋድ ነገድ ቤተ ሰቦች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ተቀብለዋልና።

15. እነዚህ ሁለቱ ነገዶችና እኩሌታው ነገድ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ፣ ከኢያሪኮ ማዶ በፀሓይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።”

16. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

17. “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤

18. ምድሪቱን በማከፋፈሉ እንዲረዱም ከየነገዱ አንዳንድ መሪ ውሰዱ።

19. ስማቸውም ይህ ነው፤ከይሁዳ ነገድ፣ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤

20. ከስምዖን ነገድ፣የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፤

21. ከብንያም ነገድ፣የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፤

22. የዳን ነገድ መሪ፣የዩግሊ ልጅ ቡቂ፤

23. የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ነገድ መሪ፣የሱፊድ ልጅ አኒኤል፤

24. የዮሴፍ ልጅ የኤፍሬም ነገድ መሪ፣የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 34