ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 34:10-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. “ ‘ለምሥራቁ ድንበራችሁም እንደዚሁ ከሐጸርዔናን እስከ ሴፋማ ምልክት አድርጉበት።

11. ወሰኑም ከሴፋማ አንሥቶ ከዓይን በስተ ምሥራቅ እስካለው እስከ ሪብላ ቊልቊል ይወርድና ከኪኔሬት ባሕርሀ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ሸንተረሮች ድረስ ይዘልቃል።

12. ከዚያም ወሰኑ የዮርዳኖስን ወንዝ ተከትሎ መጨረሻው የጨው ባሕር ይሆናል።“ ‘እንግዲህ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋር ምድራችሁ ይህች ናት።’ ”

13. ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ደልድሉ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለዘጠኙና ለግማሹ ነገድ እንድትሰጥ አዞአል፤

14. የሮቤል ነገድ ቤተ ሰቦች፣ የጋድ ነገድ ቤተ ሰቦች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ተቀብለዋልና።

15. እነዚህ ሁለቱ ነገዶችና እኩሌታው ነገድ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ፣ ከኢያሪኮ ማዶ በፀሓይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።”

16. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

17. “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤

18. ምድሪቱን በማከፋፈሉ እንዲረዱም ከየነገዱ አንዳንድ መሪ ውሰዱ።

19. ስማቸውም ይህ ነው፤ከይሁዳ ነገድ፣ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤

20. ከስምዖን ነገድ፣የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፤

21. ከብንያም ነገድ፣የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፤

22. የዳን ነገድ መሪ፣የዩግሊ ልጅ ቡቂ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 34