ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:7-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተ ምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ።

8. ከፊሀሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጒዘው በማራ ሰፈሩ።

9. ከማራ ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደነበሩበት ወደ ኤሊም መጥተው በዚያ ሰፈሩ።

10. ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ።

11. ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።

12. ከሲን ምድረ በዳ ተነሥተው በራፍቃ ሰፈሩ።

13. ከራፍቃ ተነሥተው በኤሉስ ሰፈሩ።

14. ከኤሉስ ተነሥተው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውሃ አልበረም።

15. ከራፊዲም ተነሥተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።

16. ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ።

17. ከቂብሮት ሃታቫ ተነሥተው በሐጼሮት ሰፈሩ።

18. ከሐጼሮት ተነሥተው በሪትማ ሰፈሩ።

19. ከሪትማ ተነሥተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ።

20. ከሬሞን ዘፋሬስ ተነሥተው በልብና ሰፈሩ።

21. ከልብና ተነሥተው በሪሳ ሰፈሩ።

22. ከሪሳ ተነሥተው በቀሄላታ ሰፈሩ።

23. ከቀሄላታ ተነሥተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ።

24. ከሻፍር ተራራ ተነሥተው በሐራዳ ሰፈሩ።

25. ከሐራዳ ተነሥተው በማቅሄሎት ሰፈሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33