ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:31-44 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. ከምሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።

32. ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።

33. ከሖርሃጊድጋድም ተነሥተው በዮጥባታ ሰፈሩ።

34. ከዮጥባታ ተነሥተው በዔብሮና ሰፈሩ።

35. ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።

36. ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ።

37. ከቃዴስ ተነሥተው በኤዶም ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።

38. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

39. አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር።

40. በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።

41. እነርሱም ከሖር ተራራ ተነሥተው በሴልሞና ሰፈሩ።

42. ከሴልሞና ተነሥተው በፋኖን ሰፈሩ።

43. ከፋኖን ተነሥተው በአቦት ሰፈሩ።

44. ከአቦት ተነሥተው በሞዓብ ዳርቻ በምትገኘው በኢየአባሪም ሰፈሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33