ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:23-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ከቀሄላታ ተነሥተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ።

24. ከሻፍር ተራራ ተነሥተው በሐራዳ ሰፈሩ።

25. ከሐራዳ ተነሥተው በማቅሄሎት ሰፈሩ።

26. ከማቅሄሎት ተነሥተው በታሐት ሰፈሩ።

27. ከታሐት ተነሥተው በታራ ሰፈሩ።

28. ከታራ ተነሥተው በሚትቃ ሰፈሩ።

29. ከሚትቃ ተነሥተው በሐሽሞና ሰፈሩ።

30. ከሐሽሞና ተነሥተው በምሴሮት ሰፈሩ።

31. ከምሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።

32. ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።

33. ከሖርሃጊድጋድም ተነሥተው በዮጥባታ ሰፈሩ።

34. ከዮጥባታ ተነሥተው በዔብሮና ሰፈሩ።

35. ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።

36. ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ።

37. ከቃዴስ ተነሥተው በኤዶም ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።

38. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።

39. አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33