ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብፅ ወጥተው፣ በጒዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤

2. ሙሴም በጒዞአቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጒዞም ይህ ነው፤

3. እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ።

4. በዚህ ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር (ያህዌ) ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በግብፅ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበር።

5. እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው በሱኮት ሰፈሩ።

6. ከሱኮትም ተነሥተው በምድረ በዳው ዳርቻ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ።

7. ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተ ምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ።

8. ከፊሀሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጒዘው በማራ ሰፈሩ።

9. ከማራ ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደነበሩበት ወደ ኤሊም መጥተው በዚያ ሰፈሩ።

10. ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ።

11. ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።

12. ከሲን ምድረ በዳ ተነሥተው በራፍቃ ሰፈሩ።

13. ከራፍቃ ተነሥተው በኤሉስ ሰፈሩ።

14. ከኤሉስ ተነሥተው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውሃ አልበረም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33