ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 25:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ከዚህ በኋላ ሙሴና መላው የእስራኤል ማኅበር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ እያለቀሱ ሳለ፣ አንድ እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት አንዲት ምድያማዊት ሴት ይዞ ወደ ቤተ ሰቡ መጣ።

7. የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ይህን ባየ ጊዜ ማኅበሩን ትቶ ጦሩን በእጁ በመያዝ፣

8. እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው፤ ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤

9. ሆኖም በመቅሠፍቱ የሞተው ሰው ቍጥር ሃያ አራት ሺህ ደርሶ ነበር።

10. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

11. “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደ ምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 25