ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 25:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

11. “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እኔ ለክብሬ በመካከላቸው እንደ ምቀና ስለ ቀና ቍጣዬን ከእስራኤላውያን መልሶታል፤ ስለዚህ እኔም በቅናቴ ጨርሶ አላጠፋኋቸውም፤

12. ስለዚህ እነሆ እኔ የሰላም ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር እንደማደርግ ንገረው።

13. ለአምላኩ (ኤሎሂም) ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።

14. ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 25