ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 24:18-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ኤዶም ይሸነፋል፤ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል።

19. ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።”

20. ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።”

21. ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቶአል፤

22. ያም ሆኖ ግን እናንት ቄናውያን፤አሶር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 24