ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 24:17-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. “አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል።የሞዓብን ግንባሮች፣የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቃል።

18. ኤዶም ይሸነፋል፤ጠላቱ ሴይርም ድል ይሆናል፤እስራኤል ግን እየበረታ ይሄዳል።

19. ገዥ ከያዕቆብ ይወጣል፤የተረፉትንም የከተማዪቱን ነዋሪዎች ይደመስሳል።”

20. ከዚያም በለዓም አማሌቅን አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“አማሌቅ ከሕዝቦች የመጀመሪያው ነበር፤በመጨረሻ ግን ይደመሰሳል።”

21. ቄናውያንንም አይቶ ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤“መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ጐጆህም በዐለት ውስጥ ተሠርቶአል፤

22. ያም ሆኖ ግን እናንት ቄናውያን፤አሶር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።”

23. ከዚያም ንግሩን ቀጠለ፤“አቤት! አምላክ (ኤሎሂም) ይህንሲያደርግ ማን ይተርፋል?

24. መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎችይመጣሉ፤አሦርንና ዔቦርን ይይዛሉ፤እነርሱም ደግሞ ይደመሰሳሉ።

25. ከዚህ በኋላ በለዓም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 24