ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 22:38-41 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት።

39. ከዚያም በለዓም ከባላቅ ጋር ወደ ቂርያት ሐጾት ሄደ።

40. ባላቅም ከብቶችና በጎች ሠዋ፤ ከፊሉንም ለበለዓምና ከእርሱ ጋር ለነበሩት አለቆች ሰጣቸው።

41. በማግስቱ ጠዋት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞት በኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝብ በከፊል አየ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 22