ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 21:26-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።

27. እንግዲህ ባለቅኔዎች እንደዚህ ያሉት ለዚህ ነው፤“ወደ ሐሴቦን ኑ፣ እንደ ገና ትገንባ፤የሴዎንም ከተማ ተመልሳ ትሠራ፤

28. “እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤የሞዓብን ዔር፣በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም በላ።

29. ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ!የከሞስ ሕዝብ ሆይ፤ ተደመሰስህ!ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፣ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ፣ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን አሳልፎ ሰጥቶአል።

30. “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ተደመሰሰች፤እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”

31. ስለዚህም እስራኤል በአሞራውያን ምድር ተቀመጠ።

32. ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩአቸው።

33. ከዚያም ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ በመያዝ ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዐግና መላ ሰራዊቱም ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥሟቸው ወጡ።

34. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “እርሱን ከመላው ሰራዊቱና ከምድሩ ጋር በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ሆኖ ይገዛ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ላይ ያደረግህበትን ሁሉ በእርሱም ላይ አድርግበት” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 21