ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 2:9-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።

10. “በደቡብ በኩል የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣

11. የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነው።

12. “ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣

13. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነው።

14. “ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣

15. የሰራዊቱም ብዛት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነው።

16. በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ።

17. “ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 2