ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 2:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤

2. “እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።”

3. “በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ የይሁዳ ምድብ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤

4. የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነው።

5. “ከእነዚህ ቀጥሎ የይሳኮር ነገድ ይሰፍራል፤ የይሳኮር ሕዝብ አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ሲሆን፣

6. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነው።

7. “ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣

8. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነው።

9. በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።

10. “በደቡብ በኩል የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣

11. የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነው።

12. “ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣

13. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነው።

14. “ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣

15. የሰራዊቱም ብዛት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነው።

16. በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ።

17. “ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ።

18. በምዕራብ በኩል የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 2