ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 14:38-45 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. ምድሪቱን እንዲሰልሉ ከተላኩት ሰዎች በሕይወት የተረፉት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ ነበሩ።

39. ሙሴም ይህን ለእስራኤላውያን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ክፉኛ አዘኑ።

40. በማግሥቱም ጠዋት ማልደው ወደ ተራራማው አገር ወጡ፤ እንዲህም አሉ፣ “ኀጢአት ሠርተናልና እግዚአብሔር (ያህዌ) ተስፋ ወደ ሰጠን ስፍራ እንወጣለን”።

41. ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ትእዛዝ ለምን ትጥሳላችሁ? ይህም አይሳካላችሁም!

42. እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእናንተ ጋር ስላይደለ አትውጡ፤ በጠላቶቻችሁ ድል ትመታላችሁ፤

43. አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በዚያ ያጋጥሟችኋልና። እግዚአብሔርን (ያህዌ) ስለተዋችሁትና እርሱም ከእናንተ ጋር ስለማይሆን በሰይፍ ትወድቃላችሁ።”

44. ሙሴም ሆነ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ታቦት ከሰፈር ሳይነሡ በስሜት ተገፋፍተው ብቻ ወደ ተራራማው አገር ወጡ።

45. በዚህ ጊዜ በተራራማው አገር የሚኖሩት አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወርደው ወጉአቸው፤ እስከ ሔርማ ድረስም አሳደዱአቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 14