ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 14:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያች ሌሊት ማኅበረ ሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸና አለቀሰ።

2. እስራኤላውያን በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጒረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፤ “ምነው በግብፅ ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን ባረፍነው ኖሮ!

3. እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደዚች ምድር የሚያመጣን ለምንድ ነው? በሰይፍ እንድንወድቅ ነውን? ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ታዲያ ወደ ግብፅ መመለሱ አይሻለንም?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 14