ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 12:7-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ለአገልጋዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።

8. እኔ ከእርሱ ጋር የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤እርሱ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መልክ ያያል።ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴንትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”

9. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እርሱም ትቶአቸው ሄደ።

10. ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሶአት አየ፤

11. ሙሴንም እንዲህ አለው፣ ‘ጌታዬ ሆይ፤ በስንፍናችን የሠራነውን ኀጢአት እባክህ አትቊጠርብን።

12. እርሷንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ።”

13. ስለዚህም ሙሴ፣ “አምላክ (ኤሎሂም) ሆይ፤ እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጮኸ።

14. እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት።

15. ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተገለለች፤ ከዚያ እስክትመለስም ሕዝቡ ጒዞውን አልቀጠለም ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 12