ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:51-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

51. ማደሪያው በሚነሣበት ጊዜ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያው በሚተከልበትም ጊዜ ሌዋውያን ያቁሙት፤ ሌላ ሰው ቢቀርብ ግን ይገደል።

52. እስራኤላውያን በየምድባቸው ድንኳናቸውን ይትከሉ፤ እያንዳንዱም ሰው በየሰፈሩና በየዐርማው ሥር ይስፈር።

53. ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።

54. እስራኤላውያንም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ይህን ሁሉ አደረጉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1