ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:42-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

42. ከንፍታሌም ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

43. ከንፍታሌም ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

44. በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው።

45. ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት በየቤተ ሰባቸው ተቈጠሩ፤

46. ጠቅላላ ቍጥራቸውም ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበር።

47. የሌዊ ነገድ ቤተ ሰቦች ግን ከሌሎች ጋር አብረው አልተቈጠሩም፤

48. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበርና፤

49. “የሌዊን ነገድ አትቍጠር፤ በእስራኤላውያንም ቈጠራ ውስጥ አታስገባው፤

50. በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በምስክሩ ማደሪያ፣ በውስጡ ባሉት በመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዙ በማናቸውም ነገሮች ላይ ኀላፊዎች ይሁኑ፤ ማደሪያውንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ይሸከሙ፤ በውስጡ ያገልግሉ፤ ድንኳናቸውንም በዙሪያው ይትከሉ።

51. ማደሪያው በሚነሣበት ጊዜ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያው በሚተከልበትም ጊዜ ሌዋውያን ያቁሙት፤ ሌላ ሰው ቢቀርብ ግን ይገደል።

52. እስራኤላውያን በየምድባቸው ድንኳናቸውን ይትከሉ፤ እያንዳንዱም ሰው በየሰፈሩና በየዐርማው ሥር ይስፈር።

53. ሌዋውያን ግን በእስራኤላውያን ማኅበረሰብ ላይ ቍጣ እንዳይወርድ ድንኳኖቻቸውን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፤ የምስክሩ ማደሪያ ድንኳን ኀላፊዎች ሌዋውያን ናቸው።

54. እስራኤላውያንም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ይህን ሁሉ አደረጉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1