ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 9:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ልጆቹም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ብልት አንድ በአንድ፣ ጭንቅላቱን ሳይቀር አምጥተው ሰጡት፤ እርሱም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።

14. የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጥቦ በመሠዊያው ላይ ካለው ከሚቃጠለው መሥዋዕት በላይ አቃጠለ።

15. አሮንም የሕዝቡን መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ የኀጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ ዐረደው፤ እንደ ፊተኛው ሁሉ ይህንም በኀጢአት መሥዋዕትነት ሠዋው።

16. የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አምጥቶ በሥርዐቱ መሠረት አቀረበው።

17. የእህል ቊርባኑን አመጣ፤ ከላዩም እፍኝ ሙሉ ወስዶ ጧት ጧት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በተጨማሪ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።

18. አሮንም ስለ ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የቀረቡትን በሬውንና አውራ በጉን ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።

19. የበሬውንና የአውራ በጉን ሥብ፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፤ ኵላሊቶቹንና የጒበቱን ሽፋን፣

20. በፍር ምባዎቹ ላይ አስቀመጡ፤ አሮንም ሥቡን በመሠዊያው ላይ አቃጠለ፤

21. ፍርምባዎቹንና የቀኝ ወርቹንም ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዘወዘው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 9