ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 8:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ማኅበሩን በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።”

4. ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰበ።

5. ሙሴም ማኅበሩን፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው” አላቸው።

6. ሙሴም አሮንንና ልጆቹን ወደ ፊት አወጣቸው፤ በውሃም አጠባቸው።

7. አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰው፤ መቀነት አስታጠቀው፤ ቀሚስ አጠለቀለት፤ ኤፉድ ደረበለት፤ በልዩ ጥበብ በተጠለፈው መታጠቂያ ኤፉዱን አስታጠቀው፤ በላዩም አሰረው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 8