ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 8:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ሙሴ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም እጃቸውን በበጉ ላይ ጫኑ።

19. ሙሴም በጉን ዐርዶ ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።

20. በጉንም በየብልቱ ቈራረጠ፤ ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሥቡን አቃጠለ።

21. ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን በውሃ አጠበ፤ ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) ባዘዘው መሠረት፣ በጉን በሙሉ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 8