ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 4:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፤

2. “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፣

3. “ ‘የተቀባውም ካህን በሕዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኀጢአት ቢሠራ፣ ስለ ሠራው ኀጢአት እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ።

4. ወይፈኑን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያቅርብ፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫን፤ በእግዚአብሔርም (ያህዌ) ፊት ይረደው።

5. የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ጥቂት ወስዶ ወደ መገናኛው ድንኳን ይግባ፤

6. ጣቱንም በደሙ ውስጥ ነክሮ ከመቅደሱ መጋረጃ ትይዩ፣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ሰባት ጊዜ ይርጨው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 4