ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 2:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ቈራርሰህ ዘይት አፍስበት፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።

7. የእህል ቊርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።

8. በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቊርባን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤

9. ከእህሉም ቊርባን ላይ ለመታሰቢያ የሚሆነውን ክፍል ያነሣና በእሳት የሚቃጠል፣ ሽታውም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።

10. የተረፈውም ቊርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ከሚቀርበው ቊርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 2