ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 2:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ ‘ማንኛውም ሰው የእህል ቊርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ዱቄቱ የላመ ይሁን፤ ዘይት ያፍስበት፤ ዕጣንም ይጨምርበት፤

2. ወደ ካህናቱም ወደ አሮን ልጆች ያምጣው። ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉ ያንሣለት፤ ዕጣኑንም ሁሉ ይውሰደው፤ ይህንም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው።

3. የተረፈውም የእህሉ ቊርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ከሚቀርበው ቊርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።

4. “ ‘በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ የእህል ቊርባን በምታቀርብበት ጊዜ፣ ከላመ ዱቄት ተዘጋጅቶ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ኅብስት ይሁን፤ አለዚያም ያለ እርሾ በስሱ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ ይሁን።

5. የእህል ቊርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ከተለወሰ ከላመ ዱቄት ይዘጋጅ።

6. ቈራርሰህ ዘይት አፍስበት፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።

7. የእህል ቊርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 2