ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 19:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ በዚህም ሁኔታ ፍሬው ይበዛላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

26. “ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ፤“ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።

27. “ ‘የራስ ጠጒራችሁን ዙሪያ አትከርከሙ፤ ጢማችሁንም አሳጥራችሁ አትቊረጡ።

28. “ለሞተ ሰው ሰውነታችሁን አትንጩ፤ በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

29. “ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኵሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 19