ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 15:30-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለፈሳሽዋ ርኵሰት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰር ይላታል።

31. “ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን እንዳያረክሱና በርኵሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

32. ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን፣ ዘሩም በመፍሰሱ ርኩስ የሆነውን ሰው ሁሉ፣

33. በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 15