ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 9:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ባሮች ብንሆንም፣ አምላካችን ግን ባሮች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ነገር ግን በፋርስ ነገሥታት ፊት ቸርነቱን አሳየን፤ የአምላካችንን ቤት እንደ ገና እንድንሠራና ፍርስራሾቿን እንድንጠግን አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የመከላከያ ቅጥር ሰጠን።

10. “አሁን ግን አምላካችን ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዞችህን አቃለናልና፤

11. ያቃለልነውም በባሮችህ በነቢያት አማካይነት፣ ‘ለመውረስ የምትገቡባት ምድር በሕዝቦቿ ርኵሰት ተበክላለች፤ ከዳር እስከ ዳርም በአስጸያፊ ድርጊታቸውና በርኵሰታቸው ተሞልታለች፣

12. ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ። ብርቱዎች እንድትሆኑ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት እንድታወርሱ ከእነርሱ ጋር ምንም ዐይነት ውል አታድርጉ’ ብለህ የሰጠኸውን ትእዛዝ ነው።

13. “ይህ ሁሉ የደረሰብን በክፉ ሥራችንና በብዙ በደላችን ምክንያት ነው፤ አምላካችን ሆይ፤ አንተ ግን እንደ በደላችን ብዛት አልቀጣኸንም፤ ይልቁንም ቅሬታን ተውህልን።

14. ታዲያ ትእዛዞችህን እንደ ገና ተላልፈን እንዲህ ያለውን አስጸያፊ ድርጊት ከሚፈጽሙ ሕዝቦች ጋር መጋባት ተገቢ ነውን? አንተስ ቅሬታ እስከማይኖር ወይም አንድም ሰው እስከማይድን ድረስ ተቈጥተህ አታጠፋንምን?

15. የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛም በዚህ ዕለት ተርፈን በሕይወት አለን። እነሆ፣ በፊትህ ከነበደላችን ቀርበናል፤ ከበደላችን የተነሣ ግን በፊትህ ሊቆም የሚችል ማንም የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 9