ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 2:67-70 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

67. 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው።

68. በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት በደረሱ ጊዜ፣ አንዳንድ የቤተ ሰብ መሪዎች በቀድሞው ቦታ እንደ ገና ለሚሠራው የእግዚአብሔር ቤት በበጎ ፈቃድ ስጦታ አደረጉ።

69. እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

70. ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 2